Kigali, Rwanda | As part of its High-Level Women’s Training Programme, the African Women Peace and Security Institute (AWPSI) conducted a two-day peacebuilding and reconciliation peer exchange in Kigali, Rwanda, from 30 September to 1 October 2026.

The high-level women trainees have been divided into two peer-learning groups. The first group has completed its exchange visit to Rwanda, while the second group will undertake a similar learning exchange in Kenya in the near future. The two exchanges are designed to expose participants to African experiences and approaches to peacebuilding, reconciliation, women’s participation, mediation and transitional justice.

During the Rwanda exchange, the delegation engaged with women’s organisations and peacebuilding institutions, explored Rwanda’s Home-Grown Solutions, visited the Kigali Genocide Memorial, and heard women’s lived experiences of survival, reconciliation and reintegration.

The forthcoming Kenya exchange will provide the second group with an opportunity to explore relevant experiences and practices in the Kenyan context.

The objective of the exchanges is not to replicate models from Rwanda or Kenya, but to enable the trainees to critically reflect on lessons from both countries and identify approaches that can be adapted to Ethiopia’s own context.

Following the two exchanges, the Rwanda and Kenya groups will come together to share their experiences, compare lessons, and jointly develop practical recommendations and Ethiopia-specific adaptations for strengthening women’s leadership and participation in peacebuilding and conflict prevention.

The initiative reflects AWPSI’s commitment to developing a new generation of high-level African women leaders who can translate regional learning and experience into practical approaches for advancing peace and security in Ethiopia and beyond.

የአፍሪካ ሴቶች ሰላምና ደህንነት ኢንስቲትዩት (AWPSI) እያካሄደ ባለው የከፍተኛ ደረጃ የሴቶች ሥልጠና ፕሮግራም አካል፣ ከመስከረም 20–21፣ 2019 ዓ.ም. በኪጋሊ፣ ሩዋንዳ የሁለት ቀናት የሰላም ግንባታና የእርቅ የልምድ ልውውጥ አካሂዷል።

የከፍተኛ ደረጃ የሴቶች ሥልጠና ተሳታፊዎች በሁለት የጋራ ትምህርትና ልምድ ልውውጥ ቡድኖች ተከፍለዋል። የመጀመሪያው ቡድን የሩዋንዳ የልምድ ልውውጥ ጉብኝቱን አጠናቋል፤ ሁለተኛው ቡድን ደግሞ በቅርቡ ተመሳሳይ የልምድ ልውውጥ ጉብኝት ወደ ኬንያ ያደርጋል። ሁለቱም የልምድ ልውውጦች ተሳታፊዎች በሰላም ግንባታ፣ በእርቅ፣ በሴቶች ተሳትፎ፣ በሽምግልና እና በሽግግር ፍትሕ ዙሪያ ያሉ የአፍሪካ ልምዶችንና አቀራረቦችን እንዲያውቁ የሚያስችሉ ናቸው።

በሩዋንዳ በተካሄደው የልምድ ልውውጥ የልዑካን ቡድኑ ከሴቶች ድርጅቶችና ከሰላም ግንባታ ተቋማት ጋር ውይይት አድርጓል። በተጨማሪም የሩዋንዳን የአገር በቀል መፍትሔዎች (Home-Grown Solutions) ተሞክሮ ተመልክቷል፣ የኪጋሊ የዘር ጭፍጨፋ መታሰቢያን ጎብኝቷል፣ እንዲሁም በሕይወት የተረፉ ሴቶች፣ በእርቅ እና በመልሶ መቋቋም ያሳለፉትን የሕይወት ተሞክሮ አዳምጧል።

በቅርቡ የሚካሄደው የኬንያ የልምድ ልውውጥ ሁለተኛው ቡድን በኬንያ ያሉ ተዛማጅ ልምዶችንና ተግባራዊ አሠራሮችን እንዲመለከት ዕድል ይሰጠዋል።

የእነዚህ የልምድ ልውውጥ ጉብኝቶች ዓላማ ከሩዋንዳ ወይም ከኬንያ ያሉ ሞዴሎችን በቀጥታ መቅዳት ሳይሆን፣ ተሳታፊዎች ከሁለቱም አገራት የሚገኙ ተሞክሮዎችን በጥልቀት እንዲመለከቱ፣ ትምህርቶችን እንዲወስዱ እና ከኢትዮጵያ አውድ ጋር ሊስማሙ የሚችሉ አቀራረቦችን እንዲለዩ ማስቻል ነው።

ሁለቱም የልምድ ልውውጥ ጉብኝቶች ከተጠናቀቁ በኋላ፣ የሩዋንዳውና የኬንያው ቡድኖች በመገናኘት ያገኙትን ልምድ ይጋራሉ፣ የተለያዩ ትምህርቶችን ያነጻጽራሉ፣ እንዲሁም የሴቶችን አመራርና በሰላም ግንባታ እና በግጭት መከላከል ያላቸውን ተሳትፎ ለማጠናከር በኢትዮጵያ አውድ ሊተገበሩ የሚችሉ ተግባራዊ ምክረ ሐሳቦችንና ማስማማት የሚገባቸውን አቀራረቦች በጋራ ያዘጋጃሉ።

ይህ ተነሳሽነት AWPSI በከፍተኛ ደረጃ ተተኪ የአፍሪካ ሴት መሪዎችን ለማብቃት ያለውን ቁርጠኝነት ያሳያል። ተሳታፊዎቹ ከቀጠናዊ ልምዶችና ትምህርቶች በመነሳት በኢትዮጵያና በአፍሪካ ሰላምና ደህንነትን ለማስፋፋት ተግባራዊ አቀራረቦችን እንዲያዳብሩ ያግዛል።

Categories AWPSI

Leave a Comment