የአፍሪካ ሴቶች ሰላምና ደህንነት ኢንስቲቱዩት በትግራይ ክልል ማይጨው ከተማ፣ ታደለ ሆቴል ከግንቦት27-29 ቀን 2017 ዓ.ም. በማህበረሰብ ደረጃ የሚሰጥ የ3 ተከታታይ ቀናት የአቅም ግንባታ የሁለተኛ ቀን ስልጠና ቀጥሎ ውሏል።

“የሴቶች ሰላምና ደህንነት ግንባታን የተጠናከረ አገራዊ አጀንዳ አድርጎ መገንባት”/BuildingLocalization and Resilience for the Women’s Peace and Security Agenda in
Ethiopia/ በሚል ፕሮጀክት ስር በሰላም ተልዕኮ፣ በግጭት አፈታትና በሰላም ግንባታ አተገባበር ላይ በማህበረሰብ ደረጃ የሚሰጥ የ3 ተከታታይ ቀናት የአቅም ግንባታ ስልጠና በዛሬው እለት ግንቦት 28 ቀን 2017 ዓም ቀጥሎ ውሏል፡፡
በዛሬው እለትም ስለ 1. የግጭት መተንተኛ ዘዴዎችና አስፈላጊነታቸው፣ 2. የግጭት ትንተና አይነቶች፣ 3. የግጭት ተዋንያንን መለየት፣ የሚሉ ርዕሰ ጉዳዮችን በድራማ፣ በጨዋታና በቡድን ስራ መልክእጅግ በጣም አነቃቂና አሳታፊ በሆነ መልኩ ስልጠናው ተሰጥቷል፡፡ በነገው እለት የስልጠው የመጨረሻ ርእሶችን በመዳሰስ የመዝጊያ ፕሮግራሞችን በማካሄድ የሚጠቃለል ይሆናል፡

የአፍሪካ ሴቶች ሰላምና ደህንነት ኢንስቲቱዩት በትግራይ ክልል ማይጨው ከተማ
Categories AWPSI

Leave a Comment