የአፍሪካ ሴቶች ሰላምና ደህንነት ኢንስቲትዩት በኦሮሚያ ክልል ነቀምት ከተማ፣ ሴናፍ ሆቴል ከሚያዚያ 13-16 ቀን 2018 ዓ.ም. በማህበረሰብ ደረጃ የሰጠው የ4 ተከታታይ ቀናት የአቅም ግንባታ ስልጠና ተጠናቀቀ።
“የሴቶች ሰላምና ደህንነት አጀንዳን በተጠናከረና አካባቢያዊ በሆነ መልኩ የመገንባት ምዕራፍ ሁለት ፕሮጀክት (Building Localization and Resilience for the Women’s Peace and Security Agenda in Ethiopia Project – Phase II)“ በሚል ርዕስ በሰላም ተልዕኮ፣ በግጭት አፈታትና በሰላም ግንባታ አተገባበር ላይ በማህበረሰብ ደረጃ ሲሰጥ የነበረው የ4 ተከታታይ ቀናት የአቅም ግንባታ ስልጠና በዛሬው እለት ሚያዚያ 16 ቀን 2018 ዓ.ም. ተጠናቅቋል፡፡ ሞቅ ያለ የመወያያና የእርስበርስ ክርክር በሆነ ርዕስ ስልጠናው ከተጠናቀቀ በሁዋላ፣ ከሰልጣኞች አስተያየት ተሰብስቧል። ሰልጣኖችም፣ ወደ አካባቢያቸው ሲሄዱ ስልጠና መስጠት የሚያስችል መሠረታዊ ክህሎት እንደያዙ ጠቅሰዋል።
የኢንስቲትዩቱ ክትትልና ቁጥጥር ባለሙያ የሆኑት አቶ ሙሳ ዳውድ ” የወደፊት አላማችን ከሌሎች ጎረቤት ክልሎች ጋር የሰላም አውደ ጥናት አካሂደን፣ በአንድነት የተቀናጀ የሰላም ግንባታ ተሳታፊዎች እንድትሆኑ ነው” በማለት ገልፀው ስልጠናው በይፋ ተጠናቅቋል።




Views Today : 1
Views Yesterday : 4
Views This Month : 97
Views This Year : 1513
Total views : 1758