የአፍሪካ ሴቶች ሰላምና ደህንነት ኢንስቲትዩት በኦሮሚያ ክልል ነቀምት ከተማ፣ ሴናፍ ሆቴል ከሚያዚያ 13-16 ቀን 2018 ዓ.ም. በማህበረሰብ ደረጃ የሚሰጥ የ4 ተከታታይ ቀናት የአቅም ግንባታ ስልጠና ማካሄድ ጀምሯል።
“የሴቶች ሰላምና ደህንነት አጀንዳን በተጠናከረና አካባቢያዊ በሆነ መልኩ የመገንባት ፕሮጀክት – ሁለተኛ ምዕራፍ /Building Localization and Resilience for the Women’s Peace and Security Agenda in Ethiopia Project – Phase II/” በሚል ርዕስ በሰላም ተልዕኮ፣ በግጭት አፈታትና በሰላም ግንባታ አተገባበር ላይ በማህበረሰብ ደረጃ የሚሰጥ የ4 ተከታታይ ቀናት የአቅም ግንባታ ስልጠና በዛሬው እለት ሚያዚያ 13 ቀን 2018 ዓ.ም. በነቀምት ከተማ ተጀምሯል፡፡ ስልጠናው ከመጀመሩ በፊት የፕሮጀክቱ ማስጀመሪያ የግማሽ ቀን አውደ ጥናት ተካሂዷል፡፡ የፕሮጀክቱ ማስጀመሪያ የግማሽ ቀን አውደ ጥናት ከተካሄደ በሁዋላ፣ በአሰልጣኝ በእምነት በሃይሉ አማካኝነት የስልጠና ተሳታፊዎች በተለየ አቀራረብና ዘዴ የእርስ በርስ ትውውቅ እንዲያደርጉ ተደርጓል፡፡ 29 ሰልጣኖች ከየዞኑ ወረዳዎች የተውጣጡ ሲሆን፣ በየአካባቢያቸውም በሰላምና ደህንነት ላይ የዳበረ ተሳትፎ በማድረግ ልምድ ያካበቱና ወደየወረዳቸውም ሲሄዱ ተፅዕኖ መፍጠር የሚችሉ ናቸው። ከስልጠና ተሳታፊዎች የእርስ በርስ ትውውቅ በኋላ የቅድመ ስልጠና ፈተናን በግል መለያ ኮድ እንዲሞሉ በማድረግ ስልጠናው መካሄድ ቀጥሏል።

Views Today : 4
Views Yesterday : 2
Views This Month : 96
Views This Year : 1512
Total views : 1757