የአፍሪካ ሴቶች ሰላምና ደህንነት ኢንስቲትዩት በዛሬው ዕለት ” በኢትዮጵያ የሰላም ስርዓተ ትምህርት እንዲቀረፅ ውትወታ ለማድረግ የተዘጋጀ የባለድርሻ አካላት የምክክር አውደ ጥናት በኢንተር ላግዠሪ ሆቴል እያካሄደ ይገኛል።
በዛሬው ዕለት ሰኔ 5 ቀን 2017 ዓ.ም. የአፍሪካ ሴቶች ሰላምና ደህንነት ኢንስቲትዩት፣ በኢትዮጵያ የሰላም ስርዓተ ትምህርት እንዲቀረፅ ውትወታ ለማድረግ የተዘጋጀ የባለድርሻ አካላት የምክክር አውደ ጥናት በኢንተር ላግዠሪ ሆቴል የአንድ ቀን መድረክ አዘጋጅቷል።
አውደጥናቱን በንግግር የከፈቱት የኢንስቲትዩቱ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዳይሬክተር አምባሳደር ቆንጂት ሥነጊዮርጊስ ” የሰላም ትምህርትን ከሥር ጀምረን መስጠት፣ የሰላም ዘርን በመዝራት አካታችና የሚከባበር ማህበረሰብ ለመፍጠር አጋዥ ነው” በማለት ጠቅሰዋል።
ከሰላም ሚኒስቴር የሚኒስትር ዲኤታው ዶ/ር ከይረዲን ተወካይ አቶ ወንድወሰን መኮንንም ” ሰላም ለአገር ግንባታ መሠረት ስለሆነ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤታችን ከአፍሪካ ሰላምና ደህንነት ኢንስቲትዩት ጋር በቀጣይነት የመሥራት ከፍተኛ ፍላጎት አለው” በማለት ተናግረዋል። ከሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የሚኒስትር ዲኤታዋ ክብርት ሂክማ ከይረዲን ተወካይ ሆነው የተገኙት አቶ ሰለሞን አስፋውም፣ አምባሳደር ቆንጂትና አምባሳደር ታደለች ቀደምት ተግባሮቻቸው ለሴቶች ያለውን አርአያነት ገልፀው፣ አሁንም እያከናወኑ ላሉት ተግባራት ያላቸውን አክብሮትና ምስጋና አቅርበዋል። የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴርም በአብሮነት እንደሚሠራ ተናግረዋል።
በመቀጠልም፣ የሰላም ትምህርት በሥርዓተ ትምህርት ውስጥ እንዲቀረፅ ከሚካሄደው ውትወታ ጋር በተያያዘ የዳሰሳ ጥናት ያካሄዱት ለሃገር የማማከርና ቢዝነስ ኩባንያ የዳሰሳ ጥናቱን አቅርቦ ውይይት ይካሄድበታል። በተከታይም ከባለድርሻ አካላት የተውጣጡ አወያዮች (ፓናሊስቶች) ገለፃ መነሻነት፣ ውይይት የሚካሄድ ይሆናል።
በዚህ በዛሬው አውደ ጥናት ላይ ተመርኩዞም፣ ተከታይ አውደ ጥናት ከተካሄደ በኋላ፣ ስልታዊ ሰነድ ( strategic document) እንደሚዘጋጅ ይጠበቃል።






Views Today : 4
Views Yesterday : 2
Views This Month : 96
Views This Year : 1512
Total views : 1757