ከሁሉም የአገራችን ክልሎች የተመረጡ 37 ተሳታፊዎች በዚህ ስልጠና የሚሳተፉ ሲሆን ከተሳታፊዎቹ መካከል 31ዱ ሴቶች 6ቱ ደግሞ ወንዶች ናቸው። ይህንን ስልጠና በማሰልጠን ለማመቻቸት 2 የአፍሪካ ሴቶች ሰላምና ደህንነት ኢንስቲትዩት የመካከለኛ ደረጃና የአሰልጣኖች ስልጠና ፍሬዎች ሲሆኑ፥ ለሚቀጥሉት ሶስት ቀናት ስልጠናውን በማስተባበርና በመምራት የሚቆዩ ይሆናል።
መድረኩ በአስተባባሪዋ ወ/ሮ ማህደር ዳዲ የእንኳን ደህና መጣቹ መልእክትና በዩኤን ውመን ተወካይ አቶ ነጋ ገርባባ የቁልፍ ንግግር ተጀምሮ በአምባሳደር ታደለች ሀ/ሚካኤል የመክፈቻ ንግግር በይፋ ተጀምሯል።
በአጠቃላይ ስልጠናው በዋነኝነት በግጭት አፈታት ሂደትና ትርጓሜ፣ የግጭት አይነቶች፤የግጭት አፈታት ላይ የሴቶች ሚና እና ተያያዥ የሆኑ ጉዳዮች ላይ አተኩሮ ስለአሸማጋይነትና አደራዳሪነት እንዲሁም የሴቶች ተሳትፎና ሚና የሚዳስስ ይሆናል። A total of 37 participants selected from all regions of the country are taking part in this training. Among them, 31 are women and 6 are men. The training is being facilitated by two graduates of the African Women Peace and Security Institute’s mid-level and Training of Trainers (ToT) programs, who will coordinate and lead the sessions over the next three days.
The program officially opened with a welcome message delivered by the coordinator, W/ro Mahder Dadi, followed by a keynote speech from the UN Women representative, Ato Nega Gerbaba, and was formally launched with an opening address by Ambassador Tadelech H/Mikael.


Views Today : 4
Views Yesterday : 2
Views This Month : 96
Views This Year : 1512
Total views : 1757