በአፍሪካ ሴቶች ሰላምና ደህንነት ኢንስቲትዩት ለሁለተኛ ዙር በትግራይ ክልል, ሽሬ ከተማ, ግደይ ሆቴል የሚሰጠውን የሴት ተደራዳሪዎችና አሸማጋዮች የሰላም ግንባታ ስልጠናና ግምገማ ፕሮግራም በዛሬው ዕለት ጀመረ። በታህሳስ ወር በአክሱም ከተማ የተደረገውን የመጀመርያ ዙር ስልጠና መሰረት በማድረግ የዕለቱ ፕሮግራም ያለፈውን በመከለስና በማስታወስ የተጀመረ ሲሆን የስልጠናው ተሳታፊዎች በቡድን በመሆን ውይይት አድርገው አጠቃላይ የሰብሰባውን ጭብጥ ሃሳብ በዝርዝር አቅርበዋል። ፕሮግራሙ በነገም ዕለት የሚቀጥል ሲሆን የስልጠናው ተሳታፊዎች ከመጀመርያው ዙር ስልጠና ቡሗላ ለአከባቢያቸው ሰላም ያበረከቱትን አስተዋፆ የሚያቀርቡ ይሆናል።

Views Today : 1
Views Yesterday : 4
Views This Month : 97
Views This Year : 1513
Total views : 1758