የአፍሪካ ሴቶች ሰላምና ደህንነት ኢንስቲትዩት የሰላም ትምህርትን በኢትዮጽያ ብሔራዊ ሥርዓተ- ትምህርት ውስጥ እንዲካተት የሚወተውት አውደ ጥናት አካሄደ።
አውደ ጥናቱም ለሥርዓተ-ፆታ ጉዳዮች ትኩረት የሚሰጥ እና ሁሉንም አካታች የሆነ የሰላም ትምህርት ሥርዓተ-ትምህርት በመላው ኢትዮጵያ እንዲቀረፅ በሚቻልበት ሁኔታ ከባለድርሻ አካላትጋር መክሯል፡፡ ፕሮጀክቱ ከህዝብ መሰረት ካለው የድጋፍ ሥራ ወደ ተቋማዊ ማሻሻያ በመሸጋገር፣ ሴቶችን እና የአካባቢውን ማህበረሰቦች በሰላም ግንባታ ጥረቶች ውስጥ የበኩላቸውን ጉልህ ሚና እንዲያደረጉ ያለመ ነው።
የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታ የሆኑት አየለች እሸቴ የሰላም ትምህርት በሥርዓተ- ትምህርት ይዘት መካተት ብቻ በቂ አይደለም የሚል ምልከታ አለኝ ብለዋል። አክለውም ሚኒስቴር ዲኤታዋ ተማሪዎች የሰላምን ትምህርት ማወቅ ብቻ ሳይሆን በእለት ተዕለት ህይወታቸው ተግባራዊ ማድረግ የሚችሉበትን ዕውቀት፣ ክህሎት ፣ አመለካከት እንዲሁም ባህሪይ ማዳበር ይኖርባቸዋልም ብለዋል።
በአውደ ጥናቱ ላይም የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉት የአፍሪካ ሴቶች ሰላምና ደህንነት ኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ታደለች ሃይለሚካኤል በበኩላቸው የሰላም ትምህርት በኢትዮጽያ ሥርዐተ- ትምህርት ማዘጋጀት፣ ማስተዋወቅ እንዲሁም ማካተት የአንድ ተቋም ጥረት ብቻ በቂ እንዳልሆነ ገልፀው የሁሉንም ትብብርና የጋራ ባለቤትነትንም ይጠይቃል ሲሉ አፅኖት ሰጥተው ተናግረዋል። የአፍሪካ ሴቶች ሰላምና ደህንነት ኢንስቲትዩት በሶስት አመታት ቆይታው ውስጥ ተጨባጭ በሆነ መልኩ ዘርፈ-ብዙ የውትወታ ስራዎችን ሲያከናውን ቆይቷል፥ በዚህም በዳሰሳ ጥናት እና በማስረጃ ላይ የተመሰረቱ የሰላምን ትምህርት አስፈላጊነት የሚያረጋግጡ ግምገማዎች፣ በአምስት የሀገር ውስጥ ቋንቋዎች የተተረጎሙ ቡክሌቶችና ብሮሸሮችን አዘጋጅቶ አሰራጭቷል፣ በተጨማሪም ከመደበኛው አውደ ጥናት ባሻገርም በማህበረሰብ ደረጃ የሰላም መልዕክቶችን ለማህበረሰቡ ለማድረስ ያለመ የማህበረሰብ ሬድዮ ስርጭት በተለያዩ ቋንቋዎች ተላልፈዋል።

Views Today :
Views Yesterday : 2
Views This Month : 89
Views This Year : 1505
Total views : 1750