የአፍሪካ ሴቶች ሰላምና ደህንነት ኢንስቲትዩት (AWPSI) በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን የሴት አሸማጋዮችን ሀገራዊ ትስስር ለማጠናከር ያዘጋጀው የከፍተኛ ደረጃ ስልጠና ለሁለተኛ ቀን በተሳካ ሁኔታ ቀጥሏል።
በዛሬው የስልጠና መርሃ ግብር ተሳታፊዎች በግል ሕይወታቸው፣ በሙያቸው እና በማኅበረሰባቸው ውስጥ በሰላም ግንባታና በግጭት አፈታት ሂደት ያጋጠሟቸውን ተግዳሮቶች እንዲሁም ያካበቷቸውን መልካም ተሞክሮዎች በመጋራት ከፍተኛ የመማማር እና የልምድ ልውውጥ አድርገዋል።
በስልጠናው ወቅትም ተሳታፊዎች በግጭት አፈታት፣ በሽምግልና እና በድርድር ሂደቶች ያላቸውን ዕውቀትና ክህሎት ለማጎልበት በተዘጋጁ የጉዳይ ጥናቶች (Case Studies) ላይ በቡድን በመወያየትና በመተንተን ተግባራዊ የመማር ልምድ አግኝተዋል።
በተጨማሪም በእውነተኛ ታሪኮች ላይ የተመሠረቱ አነቃቂ እና አስተማሪ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን በመመልከት በላያቸው ዙሪያ ሀሳብ ተለዋውጠዋል። በተለይም በጎንደር በተካሄደው የይቅርታ፣ የመማማር እና የክልሎች ተሳታፊዎች መስተጋብር ፕሮግራም ላይ የተቀረጸውን ተንቀሳቃሽ ምስል በመመልከት መልካም ትውስታዎቻቸው ዳግም እንደታደሱ ገልጸዋል።
ስልጠናው በተሞክሮ ልውውጥ፣ በጋራ መማማር እና በተግባር ላይ የተመሠረተ ልምምድ አማካይነት የተሳታፊዎችን የሽምግልናና የሰላም ግንባታ አቅም ይበልጥ ለማጠናከር በሚያስችል መልኩ ቀጥሏል።

Views Today : 4
Views Yesterday : 2
Views This Month : 96
Views This Year : 1512
Total views : 1757