በዚህ አውደ ጥናት የትግራይ፣ የአማራና የአፋር የሰላም ግንባታና ግጭት አፈታት ዙሪያ ላይ ማህበረሰብ አቀፍ ስልጠና የወሰዱ የሶስቱም ክልል ተሳታፊዎች በተገኙበት አጠቃላይ ከአፋር 7 ተሳታፊዎች፣ ከአማራ ክልል 10 ተሳታፊዎችና ከትግራይ 10 ተሳታፊዎች ተገኝተዋል፡፡
የአፋርና ትግራይ ክልል ተሳታፊዎች ወደ ጎንደር ከተማ ለመግባት አውሮፕላን ማረፊያ በደረሱ ጊዜ የአማራ ከልል ተሳታፊዎች የአበባ ጉንጉን በመስጠት አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡
የእለቱን ፕሮግራም በአምባሳደር ታደለችህ የሰላምታና እንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር፣ በጎንደር ከተማ ምክትል ከንቲባ የመክፈቻ ንግግር እና በአምባሳደር ዘነቡ ታደሰ ቁልፍ ንግግር ፕሮግራሙ ተጀምሯል፡፡
ሁሉም ተጋባዥ እንግዶች፣ ከሶስቱም ክልሎች በመጡ የሃይማኖት አባቶችና የየክልሉ አስተባባሪዎች አንድ ላይ ሆነው ኬክ በመቁረስ ፕሮግራሙን አስጀምረዋል፡፡
ከኬክ ቆረሳ ፕሮግራም በመቀጠል የተሳታፊዎች የርስ በርስ ትውውቅ ተደርጓል፡፡

Categories AWPSI

Leave a Comment