
የአፍሪካ ሴቶች ሰላምና ደህንነት ኢንስቲትዩት ከኤምፓቲ ፎር ላይፍ ኢንቴግሬትድ ዲቨሎፕመንት አሶሴሽን ጋር የ መግባቢያ ስምምነት ሰነድ በመፈራረም ስትራቴጂካዊ ትብብራቸውን በይፋ አፅድቀዋል። ይህም በኢትዮጵያ ብሎም በአፍሪካ ሰላምን፣ ደህንነትን፣ የፆታ እኩልነትን እና አሳታፊ ልማትን ለማረጋገጥ በሚያደርጉት የጋራ ጥረት ውስጥ ትልቅ ምዕራፍ ተደርጎ ተወስዷል።
በዚህ ስትራቴጂካዊ አጋርነት አማካይነት ሁለቱ እህትማማች ተቋማት ሙያዊ ብቃታቸውን፣ ተቋማዊ አቅማቸውን እንዲሁም ሀብታቸውን በማስተባበር በሴቶች፣ ሰላም እና ደህንነት ፣ በሰላም ትምህርት፣ በግጭት መከላከል፣ በዕርቅና ሽምግልና፣ በማህበረሰብ ጽናት፣ በፆታ እኩልነት እንዲሁም በሰላም እና ልማት ቅንጅታዊ ፕሮግራሞች ዙሪያ ተፅዕኖ ፈጣሪ ሀገራዊ እና ቀጣናዊ ተፎካካሪ ስራዎችን በጋራ ያቀዳሉ፣ ይተገብራሉም።
በተጨማሪም ስምምነቱ የሴቶችን መሪነት እና በሰላም ግንባታ ሂደቶች ላይ የሚኖራቸውን ትብብር ለማጠናከር፣ እንዲሁም ዘላቂ፣ አሳታፊ እና በማህበረሰብ የሚመራ ልማትን ለማስፋፋት ያለመ የጋራ መግባቢያ ሰነድ እንደሆነም ለመረዳት ተችሏል። ለዚህም በጋራ ምርምር፣ በእውቀት ማፍራት፣ በአቅም ግንባታ፣ በፕሮግራሞች ትግበራ፣ በክትትል እና በመረጃ የተደገፈ ስልታዊ ውትወታ ዙሪያ የተቀናጀ የስራ ማዕቀፍ ይፈጥራል።

የዚህ መግባቢያ ስምምነት መፈረም ሁለቱ ተቋማት የተቀናጀ አቅም ለመገንባት፣ ስትራቴጂካዊ ግንኙነታቸውን ለማስፋት እና ተቋማዊ አጋርነታቸውን ወደ ተጨባጭ ተግባርና በሚለኩ ውጤቶች ለመቀየር ያላቸውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ነው ተብሏል። በተጨማሪም በጋራ ፍላጎቶች ላይ የተመሰረቱ ፕሮጀክቶችን እና የጋራ ጅምር ስራዎችን ለማስቀጠል ጠንካራ መደላድል ይፈጥራል ተብሎ ይገመታል።
ተቋማቱ በጥምረት አጋርነታቸውን በማጠናከር፣ የሴቶችን ድምፅ በማስተጋባት፣ የተረጋጋች፣ አሳታፊ እና ለሴቶች ምቹና አስተማማኝ የሆነች ኢትዮጵያን የመገንባት ህልምን እውን ለማድረግ በጋራ ይሰራሉ።
AWPSI Communication
Please contact us
Website https://awpsi.org.et
Email- info@awpsi.org
Phone No. +251975029003

Views Today : 1
Views Yesterday : 4
Views This Month : 97
Views This Year : 1513
Total views : 1758