በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ከተማ ለሴት አደራዳሪዎች እና አሸማጋዮች ለሁለተኛ ጊዜ የአቅም ግንባታ ስልጠና በአፍሪካ ሴቶች ሰላምና ደህንነት ኢንስቲትዩት በዛሬው ዕለት ተካሂዶ ውሏል፡፡
ተሳታፊዎች በባለፈው የአቅም ግንባታ ወቅት የተሰጠውን ስልጠና ምን ያክል እንደተረዱትእንዲሁም በተግባር ላይ በዕለት ተዕለት ህይወታቸው ላይ በምን ያህል ደረጃ እያዋሉት ይገኛሉ የሚለውን አንስተው ተወያይተዋል፡፡ተሳታፊዎች በቆይታቸው በቡድን በመሆን እና ሴቶች እና ወንዶች ከግጭት በፊት እና በኋላ ያላቸውን ሚና ተወያይተው ለአቻተሳታፊዊቻቸው አካፍለዋል፡፡
ግጭትን የመተንተንን ምንነትንና የግጭትን መተንተኛ ዘዴ በተጨማሪም ስልቶችን በሚመለከት ሙያዊ የሆነ ዘለፃ ለተሳታፊዎች ተደርጎላቸዋል፡፡
ተሳታፊዎቹ አንድ ግጭት እንዴት ተነሳ እና ለምን ተነሳ የሚሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ያስችል ዘንድ የተለያዩ አካሄዶችን በመከተል ከመንስኤዉ ግጭትን መፍታት የሚችሉበትን መንገዶችንም ሰፊ ማብራርያ ከተሰጣቸው በኋላ፤ የግጭት ደረጃዎችን መለየት፣ የግጭት ጊዜ እርዝማኔ፣ የግጭት ተሳታፊዎችን መለየት ፣ ፍላጎትን፣ ምኞትና ዘርፋቸውን መለየት የሚሉተን በቆይታቸው በዝርዝር አይተዋል በተጨማሪም ማህበረሰብ-አቀፍ መፍትሄዎችንም በቡድንና በተናጠል አንስተው ተወያይተዋል፡፡
በዚህ ቀጣይነት ያለው ድጋፍና ክትትልን ለማከናወን ያለመው ሁለተኛ ዙር ስልጠና ወቅት ሴቶች አሸማጋዮች ባጋጠሟቸውና ሊገጥሟቸው በሚችሉ ተግዳሮቶች ዙሪያና መፍትሄዎቻቸው ላይም መክረዋል።
በማህበረሰቡ ውስጥ ቀደም ሲል ያሉትን የቆዩ ባህላዊ የእርቅ ስርዓቶች በስልጠናው ከተካተቱ ዘመናዊ የግጭት መተንተኛ ስልቶች ጋር አጣጥሞ መጠቀም የመፍትሄዎቹን ተቀባይነት የበለጠ ያጎለብተዋልም ተብሏል።

Views Today : 1
Views Yesterday : 2
Views This Month : 90
Views This Year : 1506
Total views : 1751