Transforming communities from ground up

በትላንትናው ዕለት የስልጠና ክፍለ ጊዜ የተገኙ ዋና ዋና ትምህርቶችን በመገምገም የተጀመረው ይህ የሶስተኛው ቀን
በሶማሌ ክልል እየተካሄደ የሚገኘው የሴት አሸማጋዮች ስልጠና ግጭትን መከላከል፣ የቅድመ ማስጠንቀቂያ ሥርዓቶች
እና የእርቅ ሂደቶችን በተጨማሪም ባህል፣ ሰብአዊ መብቶች እና የሴቶች ተሳትፎ በሚመለከት በመወያየት ስልጠና
በዛሬው ዕለትም ቀጥሎ ውሏል።
የሰላም ስምምነት በሚካሄድበት ወቅት ስምምነቱ ውስጥ መካተት አለባቸው የተባሉትን እንዲሁም የስርዓተ-ፆታን ጉዳይ
አስፈላጊ ትኩረት መሰጠት እንደሚገባ ሙያው ገለፃ ለተሳታፊዎቹ ተደርጓል።
በማህበረሰብ ደረጃ ላይ የተመሰረተ የሰላም የሴቶች ትስስር ዘላቂነትን ለማረጋገጥ ያስችል ዘንድ የሴቶች የሰላም
ኮሚቴዎች በተሳታፊዎች ተዋቅረዋል።
በተጨማሪም ተሳታፊዎቹ በቆይታቸው በክልሉ የሰላም ግንባታ ላይ የሴቶችን ተሳትፎ ለመከታተል ያስችል ዘንድ የግል እና
የማህበረሰብ አቀፍ የድርጊት መርሃ ግብሮችን አዘጋጅተው ለሶስት ቀናት ሲካሄድ የነበረው ስልጠና በዚህ መልኩ በስኬት
ተገባዷል።

Categories AWPSI

Leave a Comment