በዛሬው ዕለት የካቲት 3 ቀን 2018 ዓ.ም. የአፍሪካ ሴቶች ሰላምና ደህንነት ኢንስቲትዩት “የኢትዮጵያ ሴቶች ሰላምና ደህንነት አጀንዳን በተጠናከረና አካባቢያዊ በሆነ መልኩ የመገንባት ፕሮጀክት – ሁለተኛ ምዕራፍ” በሚል ርዕስ ያዘጋጀውን የፕሮጀክት ማስጀመሪያ አውደጥናት በአሶሳ ከተማ ቤን አይከን አዳራሽ ውስጥ አካሂዷል።
በቀጥታ ከአዲስ አበባ በበይነ መረብ የተሳተፉት የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዳይሬክተር አምባሳደር ታደለች ኃ/ሚካኤል በመክፈቻ ንግግራቸው፣ “የዛሬው ፕሮጀክት ማስጀመሪያ አውደ ጥናት፣ በፕሮጀክቱ ዓላማ፣ ይዘትና አቅጣጫ ላይ የጋራ መግባባት ለመፍጠርና የየድርሻችንን ኃላፊነት ለማወቅ የሚያስችል እንደሚሆን አምናለሁ። የመንግሥት አካላት፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የሲቪክ ማህበረሰብ አመራሮች፣ ምሁራንና የማህበረሰብ ተወካዮች በሙሉ፣ ፕሮጀክቱ ቀጣይነት ያለውና መሬት የወረደ የሰላም ግንባታ ጥረት አጋዥ ተግባር የሚከናወንበት እንደሆነ ተገንዝባችሁ፣ ለዚህ ፕሮጀክት መሳካት የበኩላችሁን አስተዋፅዖ እንድታደርጉ አደራ አላለሁ” ብለዋል።

ጉባዔው ቀጥሎ፣ የኢንስትቲዩቱ ምርምር ክፍል ኃላፊ አቶ ማንይንገረው ሸንቁጥ የአፍሪካ ሴቶች ሰላምና ደህንነት ኢንስቲትዩት ስለሚያከናውናቸው ተግባራትና አመሠራረት፣ እንዲሁም ፕሮጀክቱን አስመልክቶ ማብራሪያ ሰጥተዋል። በመቀጠልም የቤኒሻንጉል ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ክቡር አቶ ሰንበታ ቀጄላ፣ “ሰላም የሁሉም እስትንፋስ ነው” በማለት “በተለይም በኛ ክልል በቅርብ ዓመታት የተከሰቱ ግጭቶችን በማብረድ ረገድ ሴቶች የነበራቸው ተሳትፎ ጉልህ በመሆኑ፣ የአፍሪካ ሴቶች ሰላምና ደህንነት ኢንስቲትዩት ይዞ የመጣው ፕሮጀክት ብዙ የሰላም አምባሳደር ሴቶችን የሚያፈራልን በመሆኑ በደስታ የምንቀበለው ነው” ሲሉ ገልፀዋል፡፡ አያይዘውም፣ የአፍሪካ ሴቶች ሰላምና ደህንነት ኢንስቲትዩት ለሚያደርገው በጎ ተግባር የቤኒሻንጉል ክልል በተቻለው መጠን እገዛ እንደሚያደርግ አሳውቀዋል፡፡

በመድረኩ ሌሎች የክልሉ መንግሥት ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡ የሰላም ግንባታና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ ተወካይ ክቡር አቶ ፈይሳ አያና፣ የፋይናንስ ምክትል ቢሮ ኃላፊ የሆኑት ክብርት ወ/ሮ ትግሥት ደቢሳ እና የብልፅግና ፓርቲ የሴቶች ክንፍ ኃላፊ የሆኑት ክብርት ወ/ሮ ከልቱም ባበክር በዚህ የመክፈቻ አውደ ጥናት ተገኝተው ለፕሮጀክቱ ያላቸውን አጋርነት አሳይተዋል፡፡

የኢንስቲትዩቱ ቁጥጥርና ግምገማ ባለሙያ አቶ ሙሳ ዳውድ በመንግሥት ኃላፊዎች ለተሰጠው አጋርነት ምስጋናቸውን አቅርበው፣ ቀጣዩን የሥልጠና ፕሮግራም በማስተዋወቅ የመክፈቻውን አውደጥናት አጠናቅቀዋል፡፡

ከዛሬ የካቲት 3 ቀን 2018 ዓም. ከሰዓት ጀምሮ፣ ከክልሉ የተለያዩ ወረዳዎች (ቡለን፣ ዳንጉር፣ ድባጤ፣ ግልገል በለስ፣ ማንኩሽ፣ ፓዊ፣ ወንበራ፣ ኡራ፣ ሆሞሻ፣ ኦንዱሉ፣ አብራሞ፣ ቢልዲግሉ፣ ሸርቆሌ፣ ባምባሲ፣ ኦዳ፣ ኩርሙክ፣ አሶሳ) ለተውጣጡ ተሳታፊዎች ለሚቀጥሉት አራት ተከታታይ ቀናት ሥልጠናው የሚሰጥ ይሆናል፡፡ Today, on 10 February 2026, the African Women Peace and Security Institute conducted a project launch workshop titled “Building Localization and Resilience for the Women’s Peace and Security Agenda project – Phase Two” at the Ben Icon Hotel Hall in Assosa Town, Benishangul-Gumuz Region.

Participating live via Zoom from Addis Ababa, the Institute’s Deputy Director, Ambassador Tadelech Ha/Michael, stated in her opening remarks that “today’s project launch workshop will help create a shared understanding of the project’s objectives, content, and direction, as well as clarify our respective roles and responsibilities. I call upon all government institutions, religious leaders, civil society leaders, academics, and community representatives to recognize that this project is a practical and sustainable peacebuilding effort that reaches the grassroots level, and to contribute your share toward its success.”

Following this, the Head of the Institute’s Research Department, Mr. Manyingerew Shenkut, delivered a presentation explaining the mandate, activities, and institutional framework of the African Women Peace and Security Institute, along with an overview of the project.

Subsequently, the President of the Benishangul-Gumuz Regional Supreme Court, H.E. Mr. Senbeta Kejela, emphasized that “peace is the lifeblood of everyone,” and noted that women’s participation in resolving conflicts that occurred in the region in recent years has been particularly significant. He stated that the project introduced by the African Women Peace and Security Institute is warmly welcomed, as it will help nurture many women peace ambassadors. He further affirmed that the Benishangul-Gumuz Regional Government will provide support, to the extent possible, for the Institute’s commendable work.

Other regional government officials also attended the event, including a representative of the Peacebuilding and Security Bureau, H.E. Mr. Feyisa Ayana; the Deputy Head of the Finance Bureau, H.E. W/ro Tigist Debisa; and the Head of the Women’s Wing of the Prosperity Party, H.E. W/ro Keltum Babekir. These officials expressed their partnership and support for the project during the opening workshop.

The Institute’s Monitoring and Evaluation Expert, Mr. Musa Dawud, expressed gratitude for the cooperation extended by government officials and concluded the opening workshop by introducing the upcoming training program.

Starting this afternoon, from 10 February 2026, selected participants from various woredas of the region—Bulen, Dangur, Dibate, Gilgel Beles, Mankush, Pawi, Wombera, Ura, Homosha, Ondulu, Abramo, Bildigilu, Sherkole, Bambasi, Oda, Kurmuk, and Assosa—will receive training for four consecutive days. 

Categories AWPSI

Leave a Comment