የአፍሪካ ሴቶች ሰላምና ደህንነት ኢንስቲትዩት በአመቱ በUK FCDO ፕሮጀክት ውስጥ ከያዛቸው  የማህበረሰብ ተኮር ስልጠናዎች ውስጥ የሆነው የአማራ ክልል የማህበረሰብ ተኮር ስልጠና በዛሬው ዕለት (22/05/2018 ዓም) በጎንደር ከተማ ተጀመረ።

በታህሳስ ወር 2017 ዓ.ም የተሰጠውን የመጀመሪያ ዙር ስልጠና ማእከል በማድረግ የሰልጣኞቹን የማደራደር አቅም፣ የተደራጀ ቡድናዊ አሠራራቸውና እስከአሁን የተሰሩ ስራዎችን ለመገምገምና ለማጠናከር አልሞ በሚሰጠው ስልጠና ላይ በአጠቃላይ 27 ተሳታፊዎች ተገኝተዋል። ተሳታፊዎቹ በሁለት ዞኖች (ሰሜን ጎንደርና ወልቃይት ጠገዴ) ከሚገኙ የተለያዩ ሲቪል ማህበራትን፥ ሀይማኖት ተኮር ተቋማትንና ማህበረሰብ ተኮር አደረጃጀቶች የተውጣጡ ሲሆን  20 ሴቶችና 7 ወንዶች ይገኙበታል፡፡

ከተሳታፊዎቹ ጋር በሚኖረን የሙሉ ቀን ቆይታም ባገኙት ስልጠና ምን ዕውቀት እንደጨበጡ፣ ባገኙትም ዕውቀት በአካባቢያቸው የሰላም ግንባታ ተሳትፎ ምን እንደከወኑ፣ ወደፊትም ምን ማድረግ እንደሚችሉ ውይይትና የልምድ ልውውጥ  ይካሄዳል፡፡ የአካባቢያቸውንም ይሁን በማህበረሰቡ ውስጥ የድርሻቸውን እንዲወጡ እስካሁን የተሰሩትን በማጠናከር የተሻሉ ስራዎች እንዲሰሩ ማገዝ የሚቻልበት ሁኔታ ላይ ምክክር ይደረጋል፡፡

ኢንስቲቱዩታችን መሰል ስልጠናዎችን የሚያካሂደው በየትኛውም ማህበረሰባዊም ይሁን ክልላዊ የሰላም ውይይቶች፣ ድርድሮችና ሌሎች የግጭት አፈታት ሂደቶች ውስጥ የሴቶች ተሳትፎ እንዲጎለብት ከማድረግ አንፃር የበኩላቸውን አስተዋፅዖ እንዲሚያደርጉ በመተማመን ነው። በተጨማሪም በመድረኩ የእለቱ አውደጥናት ዓላማና ግብ ገለፃ ከተደረገ በኋላ ያለፉትን የስልጠና ይዘቶች በቡድን ውይይት በማስታወስ ቀጥሏል።

The second round of community-based training and a contribution review of the trainees has begun in the Amhara Region.

One of the community-based trainings organized this year by the African Women’s Peace and Security Institute under the UK FCDO project—the Amhara Regional community-based training—officially commenced today (22/05/2018 E.C.) in Gondar city.

Building on the first round of training conducted in December 2017 E.C., this follow-up training aims to review and strengthen the trainees’ mediation capacity, their organized group-based approaches, and the peacebuilding activities carried out so far. A total of 27 participants are attending the training. The participants come from various civil society organizations, faith-based institutions, and community-based organizations located in two zones (North Gondar and Wolkait Tegede). Among them are 20 women and 7 men.

During the full-day engagement with the participants, discussions and experience-sharing sessions will be held to assess what knowledge they have gained from the training, how they have applied that knowledge to peacebuilding efforts in their communities, and what actions they can undertake going forward. Consultations will also be conducted on how to further strengthen the work done so far and support participants to play a more effective role both in their local areas and within the broader community.

Our Institute conducts such trainings with the conviction that they will enable women to make meaningful contributions by enhancing their participation in community-level and regional peace dialogues, negotiations, and other conflict resolution processes. In addition, after an explanation of the objectives and goals of the day’s program, the session continued with group discussions that revisited previous training contents.

Categories AWPSI

Leave a Comment