የአፋር ክልል ሁለተኛ ዙር የማህበረሰብ ተኮር ስልጠናና የስልጠናው ተሳታፊዎች አበርክቶ ግምገማ መካሄድ ጀመረ።
በአመቱ በUK FCDO ከተያዙት የማህበረሰብ ተኮር ስልጠናዎች ውስጥ የሆነው የአፋር ክልል የማህበረሰብ ተኮር ስልጠና በዛሬው ዕለት (19/05/2018 ዓም) በአዋሽ 7 ከተማ ተጀመረ። በነሀሴ ወር 2017 ዓ.ም የተሰጠውን የመጀመሪያ ዙር ስልጠና ማእከል በማድረግ የሰልጣኞቹን የማደራደር አቅም፣ የተደራጀ ቡድናዊ አሰራራቸውና እስከአሁን የተሰሩ ስራዎችን ለመገምገምና ለማጠናከር አልሞ የተሰጠው ስልጠና ላይ በአጠቃላይ 19 ተሳታፊዎች ተገኝተዋል። ታሳታፊዎቹ በዞን 3 ከሚገኙ የተለያዩ ሲቪል ማህበራትን፥ ሀይማኖት ተኮር ተቋማትንና ማህበረሰብ ተኮር አደረጃጀቶችን የወከሉ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ 12ቱ ሴቶች ሲሆኑ 7ቱ ተሳታፊዎች ደግሞ ወንዶች ናቸው።
ከሳታፊዎቹ ጋር በሚኖረን የሙሉ ቀን ቆይታም በየትኛውም ማህበረሰባዊም ይሁን ክልላዊ የሰላም ውይይቶች፥ ድርድሮችና ሌሎች የግጭት አፈታት ሂደቶች ውስጥ የሴቶችን ተሳትፎ እንዲጨምር ከማድረግ አንፃዕር የበኩላቸውን አስተዋፆ እንዲያደርጉ መተማመን ነው። በተጨማሪም የአካባቢያቸውንም ይሁን በማህበረሰቡ ውስጥ በዘርፉ ያለው እውቀት እንዲጎለብት የድርሻቸውን እንዲወጡ እስካሁን የተሰሩትን በማጠናከር የተሻሉ ስራዎች እንዲሰሩ ማገዝ የሚቻልበት ሁኔታ ላይ መመካከር ነው።
በመድረኩ የእለቱን ዓላማና ግብ ገለፃ ከተደረገ በኋላ ከስልጠና በኋላ በግለሰብ ደረጃ የተሰሩ ስራዎችን በመገምገም የተጀመረ ሲሆን ያለፉትን የስልጠና ይዘቶች በቡድን ውይይት በማስታወስ ቀጥሏል።


Views Today : 1
Views Yesterday : 4
Views This Month : 97
Views This Year : 1513
Total views : 1758