Workshop Image

በእናቶች ለሰላም ማህበር አዘጋጅነት የተካሄደው ስብሰባ በአፍሪካ ሴቶች ሰላምና ደህንነት ኢንስቲትዩት ድጋፍ ተደርጎለታል። በሃይማኖት አባቶች ፀሎት የተጀመረው ስብሰባ የማህበሩ ሊቀመንበር ወ/ሮ መቅደስ እናቶች ለሰላም ማህበር ለሰላም ያለውን አስተዋፅኦ ገልፀው በይፋ ተከፍቷል።

የትግራይ ሴቶች ጉዳይ ቢሮ ምክትል ሃላፊ ወ/ሮ አለማሽ ከጦርነቱ በፊት የተቋቋመው ማህበር የሚሠራውን ሥራ አድንቀው ሰላም በማውራት ሳይሆን በተግባር የሚከወን ጉዳይ መሆኑን ገልፀዋል።አክለውም በትግራይ ውስጥ ከ15,200 በላይ  የሥርአተ ፆታ ጥቃት የደረሠባቸው ሴቶች ስላሉ ወደቀያቸው እንዲመለሱ መሥራት ያስፈልጋል ብለዋል። በዚህ ወቅት እየተደረገ ያለው ተግባር እንዱቀጥል በመጠቆም  ተሳታፊዎችን ሁሉ አመሥግነዋል።

በትግራይ ክልል የብዝሃነትና የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ የሆኑት አቶ ካላዩ  የሰላም አጀንዳ ለእናቶች ከፍተኛ ነው። የትግራይ እናቶች ሰላም ይፈልጋሉ።እኒህ ሩህሩህ እናቶች ሊረዱ ይገባል። ይህንንም ለመንግሥት እንድታሳውቁልን አደራ እላለሁ በማለት መልክታቸውን አስተላልፈዋል።

የአፍሪካ ሴቶች ሰላምና ደህንነት ኢንስቲትዩት ተወካይ አቶ ማንይንገረው ሸንቁጥ በበኩላቸው  ኢንስቲትዩታቸው ከተቋቋመበት አላማ አንፃር በሴቶች ሰላምና ደህንነት ጉዳይ በትግራይና ሌሎች ክልሎች የሚሠራውን ሥራ አጠናክሮ እንደሚቀጥልና እንደ እናቶች ለሰላም ያሉትን ማህበራት እንደሚደግፍም ገልፀዋል።

ከእረፍት በኋላ “በሰላም ባህል ግንባታ የሴቶች ሚና” በሚል ርእስ ፅሁፍ ቀርቦ ውይይት ተደርጓል። በውይይቱም ከሁሉም የትግራይ ክልል ዞኖች የተወከሉት ተሳታፊዎች በንቃት ተወያይተዋል።

በቀጣዩ ቀን የሰላም ለእናቶች ማህበር አባላት ከሌሎች ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር እንደሚወያዩ ይጠበቃል።

Categories AWPSI

Leave a Comment