የአፍሪካ ሴቶች ሰላምና ደህንነት ኢንስቲትዩት በዛሬው ዕለት “በኢትዮጵያ የሰላም ስርዓተ ትምህርት እንዲቀረፅ ውትወታ ለማድረግ የተዘጋጀ ሁለተኛ ዙር የባለድርሻ አካላት የምክክር አውደ ጥናት በኢንተር ላግዠሪ ሆቴል እያካሄደ ይገኛል።
በዛሬው ዕለት ጥቅምት 6 ቀን 2018 ዓ.ም. የአፍሪካ ሴቶች ሰላምና ደህንነት ኢንስቲትዩት፣ በኢትዮጵያ የሰላም ስርዓተ ትምህርት እንዲቀረፅ ውትወታ ለማድረግ የተዘጋጀ ሁለተኛ ዙር የባለድርሻ አካላት የምክክር አውደ ጥናት በኢንተር ላግዠሪ ሆቴል የአንድ ቀን መድረክ አዘጋጅቷል።
አውደጥናቱን በንግግር የከፈቱት የኢንስቲትዩቱ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዳይሬክተር አምባሳደር ቆንጂት ሥነጊዮርጊስ “የሰላም ትምህርት በብሔራዊ ሥርአተ ትምህርት ውስጥ እንዲካተት ማድረግ በእጅጉ አስፈላጊ ነው። አላማውን ከግብ ለማድረስም ውትወታችን ይቀጥላል” በማለት ጠቅሰው አውደጥናቱን በይፋ ከፍተዋል።
ከሰላም ሚኒስቴር የሚኒስትር ዲኤታው ዶ/ር ከይረዲን ተዘራ ተወካይ፣ የሰላም ግንባታ ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ወንድወሰን መኮንንም “ያለሰላም ምንም ነገር ቅንጦት ነው። የአፍሪካ ሰላምና ደህንነት ኢንስቲትዩት ይህንን የውትወታ መድረክ ለሁለተኛ ጊዜ በማዘጋጀቱ ትልቅ ተግባር እየፈፀመ ነውና ሊመሰገን ይገባል። የሰላም ሚኒስቴር ይህንኑ አሳብ ይዞ አጀንዳው የህዝብ እንዲሆን ይሠራል” በማለት ተናግረዋል።
በመቀጠልም የኢንስቲትዩቱ ድረ ገፅ በአምባሳደር ቆንጂትና አቶ ወንድወሰን መኮንን በይፋ ተከፍቷል። ድረ ገፁን ያበለፀጉት የኢትዮ ቴክኖሎጂ አቶ በቃሉ አመኑ አጠቃላይ መግለጫ ሰጥተዋል።
በመቀጠልም፣ የሰላም ትምህርት በሥርዓተ ትምህርት ውስጥ እንዲቀረፅ ከሚካሄደው ውትወታ ጋር በተያያዘ ከመጀመሪያ ዙር (ሰኔ 5/ 2017ዓም) አውደጥናት የተገኙትን ውጤቶች በመግለፅ የለሃገር የማማከርና ቢዝነስ ኩባንያ ባልደረባ የሆኑት ወ/ት አሚን ለቡድን ውይይት መነሻ የሚሆኑ አሳቦችን አንስተው የተሳታፊዎችን ውይይት አስጀምረዋል።
አውደጥናቱ ከምሳ ሰአትም በሁዋላ የውትወታ ስልት ሰነዱ ላይ በመወያየት የሚቀጥል ይሆናል።





Views Today : 4
Views Yesterday : 2
Views This Month : 96
Views This Year : 1512
Total views : 1757